ይፋጃል

 

አርግዛና - አምጣ

ላም - እሳት ወለደች

አትልሰው - ይፋጃል

አትተወው - ልጅ ሆኗል

ጥጃ መላው ጠፍቶት -

እምቧ ራበኝ ይላል::

እማህል ቤት ሆና - ሳታደርግ አንዱንም፤

ጥጃው ሞቶ አረፈ - ቢያጣ የሚያስታምም።